In Stock

3000 ሌሊቶች

$18

Author: Andualem Arage

Categories: ,

Description

“(የ) አንዱዓለም የእስር ሕይወት መንፈሳዊና ሥነ-ልቦናዊ ሕይወት ምን እንደሚመስል እንኳን ታስረው ለማያውቁት፣ በእስር ማቀን ለወጣነው ሳይቀር በሚያስደምም መልኩ በዚህ መጽሐፉ ድንቅ አድርጎ ተርኮታል። [በርግጥ] የአንዴዓለምን መጽሐፍ እንድወደው ካደረጉኝ ከሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች አንዱና ዋነኛው ከራሱ ጋር በሚሟገት ራሱን በሚመረምር ሰው የተጻፈ መጽሐፍ መሆኑ አንዱ ነው። በዚህ መጽሐፍ የህሊና እስረኛ፣ የህሊና ስቃይ በየፈርጁ ተሰንዷል። .. በሃሰት መወንጀልና ለአመታት በግፍ መታሰር የሚወልደውን ከበደል የሚመነጭ የህሊና ሰቆቃ እናያለን። ጭኔም;| ዐ00 ሌሊቶችን በማንበቤ በስብእና የመበልጸግ ስሜት ተሰምቶኛል። ከአንድ መጽሐፍ ከዚህ በላይ ገጸ በረከት አይጠበቅም። ሁላችንም አንብበን የገጸ በረከቱ ተቋዳሾች እንሁን“።

አንዳርጋቸው ጽጌ

ጉምቱው ፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌ ስክነት-ለተሳነው የኢትዮጵ ፖለቲካ (ቅንነቱ ቢኖር) ሊያረጋጉ የሚችሉ ሦስት መጽሐፎችን አስነብቦናል፡፡ ሁለቱ የተሰናዱት እንዲህ ዐይነቶቹ ወፍራም ጥራዞች ቀርቶ፤ በብጣሽወረቅት ደብዳቤ ለመጻፍ አደገኛ በሆነበት እስር ቤት ነው። ከፖሊሶች እስከ “እስተኳሽ እስረኞችበጥብቅ በሚሰለልበት ግቢ፣ ያውም ጨለማ ቤት” የተወረወረ እስረኛ ጠንካራ ይዘት ያላቸመጽሐፍቶችን ከማዘጋጀት አልፎ፤ በድብቅ ወጥተው እንዲታተሙ ያደረገበት ምስጢር፣ የአራተኛውን መጽሐፍ ረቂቅ እስካነብ አልተገለጠልኝም ነበር።

“3000 ሌሊቶች”ቫ፣ ቀዳሚዎቹ መጽሐፍቶቹ በምን ሁኔታ ውስጥ እንደተጻፋ ይነግረናል፡፡ የቃሊቲ እስር ቤት ኀሮን በግቢው ያለን እስኪመስለን ድረስ ገላልጦ ያሳየናል፡፡ ዛሬ፣ እንደ ሲብስቴ ነጋሲ ዘመን ተረት እየመሰለ በሄደው ምርጫ #7 ጦስ የታሰሩ የቅንጅት የአመራር አባላትን አክራሞትና የይቅርታ ሂደቱን ዘግቦታል።”

ራሳቸውን የዱርየ ነፃ አውጪ ግንባር (ዱነግን ብለው የሚጠሩ በከባድ ወንጀል የተፈረደባቸው የአዲስ አበባ ልጆች፣ ለፖለቲካ እስረኛ የሚሰጡትን አክብሮትና ትብበር ዉስከ መስዋትነት የሚደርሱም አሉን አስነብቦ ያስደንቀናል።

አንዱዓለም፣ ያሳለፈውን ሕማማት እየተረከ ልባችንን በሀዘን ቢሰብረውም፣ ጥቂቶች ብቻ የታደሉትን ለሀገርና ለሕዝብ በደስታ ዋጋ የመክፍል ብርታንን አስነብቦ፣ ያጀግነናል፡፡ በጥቅሉ በኢትዮጵያ ወህኒዎች እስረኞች ምን ዐይነት ህይወት እንደሚያሳልፉ በአዝናኝ ክስተቶች፣ በእሳዛኝ አጋጣሚዎች፣ ክቡድ መልዕክት ባለቸው ቁምኀገሮች… አስደግፎ በተዋበ ብዕር ተርኮልናል። የኢትዮጵያ እስር ቤቶችን ገመና ማጥናት ለሚፈልግም ሆነ ለማኀበራዊ ሳይንስ ባለሙያ ከዚህ የተሸለ የመረጃ ምንጭ እንደሌለ ለመመስከር እደፍራለሁ።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

Reviews

There are no reviews yet.

Be the first to review “3000 ሌሊቶች”