In Stock

የአንድ ኃይል

$18

አንድ ትራፊክ ፖሊስ ሙሉ ትጥቁን አድርጎ መኪና በፍጥነት በሚርመስበት መገገድ መካከል ቆሞ የእጅ ምልክት ቢያሳይ የቱንም ያህል ልምድ ያለው ሹፌር፣ምንም አይነት የዋጋ ደረጃ ያለው መኪና፣ ለማጅ ሆነ ርካሽ መኪናን እኩል ያስቆማል፡፡ አንዲህ በዘመን ሆኖ የማያውቅ ነገር በ2012 አስተናግደናል፡፡ አንዲት ቫይረስ አለሙን በሙሉ ቀጥ አድርጋለች፡፡ ምናልባት 2ዐ12 ስሌትን የተማርንበት አመት ይመስለኛል፡፡ በአንድ አለሙ ሁሉ ቆሟል፡፡

አንድ ስንት ሆነ? አንድን ነገር ከስሙ በላይ መጠየቅ በዓላማው መጠን መጠቀም መልካም ነው፡፡ ይህች መፅሐፍ ደንብራ ለነቃቶች ተለውጣ ለጠበቀችው አለም የአንድ ኃይልን በመጠቀም የሰው ለሰው ግንኙነት ወደአቅም የሚለውጥበትን ጥበብ ታካፍላለች፡፡ የአንድ ኃይል ምንድነው? ቤቴ፣ ትዳሬ፣ ግንኙነቴ፣ ዝምድናዬ ሁሉ የአንድ ኃይልን ተጠቅሞ አቅም መሆን ይችላል? በውስጥ ገፅ መልስ እናገኛለን፡፡ ምን ይታወቃል አንድ ኮቪድ 19 ስም አውጥተን በአለም ሁሉ አንዴ ፀጥ በሉና ስሙኝ በማለት ሊያስቆም ከታመነ፡፥ አንድ ግለሰብ፣ ቤተሰብ፣ ተቋምም ሆነ ማህበር አንድ በመሆን ያለውን ሊሰማ በሚችል መጠን ለውጦ ለማቅረብ ቢተጋ እንዴት አለሙን በመድረስ መሰማት ያቅተዋል?

አንድነት ከአንድ ይወለዳል!

Categories: ,

Description

በ ህይወት አሰፋ

Reviews

There are no reviews yet.

Be the first to review “የአንድ ኃይል”