Description
ሀገር የሚመራበት ሥርዓት ሚዛኑን ጠብቆ እንዲጓዝ የሚያስችሉት ብዙ ነገሮች ይኖራሉ፤ ዋነኞቹ ግን ተቋማት ናቸው። እነዚህ ተቋማት ዐቅማቸው እየደከመ ሲሄድ በሥርዓቱ ውስጥ ግለሰቦች ጉልበታቸው እንዲፈረጥም ዕድል መፍጠሩ አይቀርም። ለምሳሌ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ዲሞክራሲ ሊወለድባቸው ገና ብዙ ትግል በሚቀራቸው ሀገራት ነጻ የፖሊቲካ እንቅስቃሴ ለማካሄድ ሜዳውን ለሁሉም ክፍት ማድረግ ብቻ አይበቃም። ሂደቱ ያለ ችግር እንዲከናወን፣ ግለሰቦች ያለመሸማቀቅና ያለጥቃት እንዲሳተፉ፣ የዲሞክራሲና የፍትሕ አካላት ሚዛን የመጠበቅ ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት ይኖርባቸዋል። ይህ ካልሆነ የሥርዓቱ ሚዛን የሚጠበቀው በግለሰቦች በጎ ፈቃድ መልካም ስብእና ላይ ተመስርቶ ይሆናል።
ኢትዮጵያችን፣ ሁሉ ዜጋ እና ሁሉም ብሄር በእኩልነት የሚኖርባት ሀገር እንድትሆን ማድረግ በእያንዳንዳችን የሚጠበቅ ትልቅ የቤት ስራ ቢሆንም፣ ይሄን ለማድረግ መጀመሪያ ሀገር ሊኖረን ይገባል። የጋራ ቤታችን በቅድሚያ በቅጡ መቆም አለበት። ውሃ ላይ እንደተጣለ ኩበት ከወዲያ ወዲህ ዥዋዣዌ በሚጫወት ቤት ውስጥ የግለሰቦች ነጻነት እና የብሄሮች እኩልነት ትርጉም አይሆረውም።
ግለሰብም ሆነ ማህበረሰብ በመልካም ሕይወትና በተደላደለ ሰላም ለመኖር ፍቅርና ይቅር ባይነት አስልፈላጊዎቹ እንጂ ቅንጦቶች አይደሉም። በፍቅር እንደመር፣ በይቅርታ እንሻገር የሚለውን መሪ ሐሳብ አምጦ የወለደውም ኢትዮጵያን ወደዚህ መልካም ሕይወትና የተደላደለ ሰላም ለመምራት ያለው ጽኑ ፍላጎት ነው።
Reviews
There are no reviews yet.