Description
አሌክስ አብርሃም በከዚህ ቀደም መጽሃፎቹ አሳምሬ አውቀዋላሁ። እንሆ ደግሞ አሁን ማለፊያ የብዕሩ የሕይወትን ማጀትና አደባባይ እንዳሻው ዕያሰሰ የሚያሳይበትን ትነቦ የማይጠገብ ዓይነተኛ የጽሁፍ በረከቶቹን ጀባ ብሎናል። እንዲህ በየግዜው እያሸተ ከሚያጎመረው የኅሊናው ማዕድ በመቋደሴ ዕድለኛ ነኝ እላለሁ። በረካ ሁን አቦ!
ደራሲ ኀይለመለኮት መዋዕል
የለሌክሰ አበርሃም ሥሪዎች ቀላል ከሚመስሉ ጉዳዮች ተነስተው በግልፅ ጉዳይ ላይ እያጠነጠኑ
ይቆዩና፡ መጨረሻ ማሰረያቸው አልየም የሆነ የታሪኩ ክፍል ላይ በወሱን እና ድንገተኛ ቃላት ፖለቲክስ፤ ታሪክ ፤ ፍልስፍና ፤ ስነልቦና ፤ እምነት ፤ ባዮሎጂ ወይም ኬምስትሪ በመሆን አጠቃላይ ታሪኩን ወዳልታሰበ ጉዳይ ይወስዱታል። ጥቃቅን ጉዳዮችን አምጥቶ ታሪኩን እያበሰራ የሚገባበት መንገድ ለአማርኛ ልበ ወለድ አዲስ ነው ብየ አስባለሁ፤ በአማርኛ ልብ ወለዶች ርዕሰ ጉዳዩን ከመጀመሪያው ጀምሮ በታሪኩ ውስጥ እያብራሩ መምጣት ነው የተለመደው። በምዕራቡ ዓለም ኢሴይን ወደ ልበ ወለድ በመቀየር ወይም አሁን በዘመኑ የገነነውን የ ኢሰይ ዘመን ኢሴይ ጋር በተቀየጡ ልበ ወለዶች ሰብሮ በመግባት የቸኩ (Czeck) ደራሲ ኩንዴራ /Milan Kundera/ ቀዳሚ ነው ለኔ። ወደ እኛ አገር ስንመጣ ደግሞ አሌክስ አብርሃም ለአገራችን ይህን አዲስ አጻጻፍ በማስተዋወቅ የመጀመሪያው ነው ማለት ይቻላል። የአሌክስ አብርሃም ስራዎች በአገራችን ስነ ጽሁፍ መጭውን የልበ ወለድ እና አጭር ልበ ወለድ መጻኢ እድል ጠቋሚዎች ናቸው።
Reviews
There are no reviews yet.