Description
የዘመኔ ጀግና እንዲህ የሚል ይመስለኛል…
“በኔ ዘመንና በጥንት አቴናውያን የቸነፈር ዘመን መካከል መሰረታዊ መመሳሰል አለ። በሁለቱም ዘመኖች ውስጥ ለነገ ተስፋ ማድረግ የሚባል ነገር የለም። ለፍቼ የሰራሁትን ቤተን ባቡር ይሁን ሰርጓጅ መርከብ በዉል ያልታወቀ ነገር ጥሶት የሚያልፍ ከሆነ ለመስራት እንዴት ላቅድ እችላለሁ? ሰባት መቶ ሺህ ብር የገዛሁትን ቤቴን በክረምት አፍርሶ ደርዘን ጃንጥላ የማይገዛ ፍራንክ ሸጎጥ አድርጎ፤ ቤተመቅደስ እንደገባች ውሻ አካልቦ የሚያባርረኝ ባለስልጣን ባለበት ሀገር ውስጥ ጎጆ ለምን እቀልሳለሁ። ጎቶች፤ ለችግር ቀኔ ያጠራቀምኩትን ብር ብጥጋብ ዘመናቸው የሚወሱብኝ ከሆነ የባንክ ደብተር የማወጠው ለምንድነው? ልጄ ብህይዎት እያለሁ እኋላ መውታ ልሆን እንደሚችል እያወቅሁ፤ “የዛሬ አመት የማሙሽ ልደት” እያልሁ የሚዘፍንበት ምክንያት ምንድነው? “ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር” ከሚለው መፈክር በስተቀር ኢትዮጵያን ለዘላለም የሚያኖራት መሰረት መፍረሱን እያወቅሁ ለሚቀጥለው አመት እንዴ ላቅድ እችላለሁ? ተው ባክህ! እኔም እንደጥንቱ አቴናውያን የሞት ፍርድ እንደተፈረደበት ሰው እኖራለሁ። የመሰቀያው ገመድ አንገቴ ውስጥ እስቲገባ ድረስ የጥንቱ ባላገር ግጥም በቃሌ እወጣለሁ።
Reviews
There are no reviews yet.