Description
“አዳም በገነት [ሳይበድል] ቢኖር መድኃኒታችን ከማርያም ባልተወለደ በተድላ ገነትም የትውልድ ዘር ባልኾነ ነበር። በውስጧ የሚያድሩት በሰማይ ሥርዓት ይኖራሉና! በገነት አፀድ የወንድና የሴት ሩካቤ የሚገባ ቢኾን ኖሮ አዳም ሚሜስቱን ባወቃት ነበር።”
አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ
“ሰውን የሚወድ እግዚአብሔር ስሰ ድኅነታችን አስቦ ለሰው ልጆች ኹለት የሕይወት መገገዶችን አዘጋጀ – ጋብቻንና ድንግልናን! ይኸውም የድንግልናን መከራ መሸከም የማይችል ሰው የጋብቻ መንገድን እንዲጠቀም ነው፡ ኾኖም ግን የጋብቻን መንገድ ሲመርጥ በጋብቻ ሕይወትና ሕፃናትን በማሳደግ ሕይወት የኖሩትን ቅዱሳንን መስሎ ልከኝነትንና- ቅድስናን መያዝ ይኖርበታል።ለወንጌል መታዘዝ ካገቡትም ካላገቡትም ከኹላችንም የሚጠበቅ ነውና፡፡ ያገባ ሰው ራሱን ስላለመግዛቱናሜስትንና የጋብቻ ሕይወትን በመፈለጉ ይቅርታ ይደረግለታል፡፡ ከዚህ ውጭ ባሉት ትእዋዙ ግን ንጽሕ ጠብቆ እንደሚኖረው እንደ መነኩሴው ይጠብቃቸው ዘንድ ግዴታ ነው፡፦
ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ
“በዚያ (በገነት) ያገቡት ኹሉ በወሲድ ምክንያት ካገኛቸው የርግማን ውጤት ጽኑ ሥቃይ፤ ልጆች በማስገኘት መከራን ከተሳተፉ በኋላ ዕረፍትን ያ፡ሉ፡፡ አሁን አነዚያ እያለቀሰች የቀበረቻቸው ሕፃናት እንደ ጠበቶች በኤደን ገነት ተስማርተው ትመለከታቸዋለች፡፡ በማዕርጋቸው የተመሰገኑ ናቸው፡፡ በውበታቸውም የተደነቁ ናቸው፤ ፍጹም ንጹሐን የኾኑት የመሳእክት ወገኖችን ይመስላሉ፡ ትዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ “በስሟ ብቻ አትጥራት፤ በአክብሮትና በቁልምጫ ስም ጥራት፤ ፈጽመህም አክብራት፡ እንዲህ ካደረግህ ክሌሎች ምስጋናን አትሻምዓ አመስግናት፡፡ በወብትዋና በአስተዋይነትዋ፤ በማንኛውም ነገር ከኹሉ በፊት እርስዋ ምርጫህ ትኹን፡፡ አመስግናትም። በዚህም በውጪ ስላሉት ነገሮች ቁብ እንዳይኖራት ከአንተ በቀር
በዓለሙ ላይ እንድትሳለቅ ማድረግ ትችህላለህ።”
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
Reviews
There are no reviews yet.