In Stock

ራስን ማወቅ

$15

Author: Roben Sharma

ትርጉም፡ ብርሃኑ በላቸው

Categories: ,

Description

ብዙ ሰዎች ራሳቸውን ሳያዉቁ ነው የሚኖሩት። ጥንካሬያችው፣ ድክመታቸው ተስፋቸውና ህልሞቻችው ምን እንደሆኑ አያውቁም። ይህን ይበልጥ ለማስረዳት የቻይናዎችን ምሳሌ መጥቀስ ያሰፈልጋል። ቻይናውያን እንደሚሉት የሰውን መልክ የሚያሳዩ ሶስት መስታውቶች አሉ።

የመጀመሪያው ራስህን እንዴት እንደምታይ የሚያሳይ ነው፣ ሁለተኛው በሌሎች ዐይን አንተ ምን እንደምትመስል የሚያሳይ ነው። ሶስተኛው ደግሞ ትክክለኛ ገጽታህን የሚያሳይህ ነው። ስለዚህ ራስህን ዕወቅ፣ እውነታውን ዕወቅ።

ፍርሃት የአሳተሳሰብ ምላሽ ነው። ፍርሃት በጊዜ ካልተወገደ ኃይልንም ያዳክማል፣ የፈጠራ ችሎታህን ያጠፋል። ዋናው አለመፍራት ነው፣ ዋናው የምትፈራውን በድፍረት መተግበር ነው። የፍርሃትን ምንነት በደንብ ተገንዘብ። ፍርሃት የአንተው ፈጠራ ነው። ልክ እንደማንኛውም የፈጠራ ውጤት ማውደምና ከአንተ ማራቅ ትችላለሕ ይህም ታላቅ የራስ መተማመን ደስት የአእምሮ ሰላምን ያጎናጽፍሃል።

በየዕለቱ ለ30 ደቂቃዎች ማንበብ በሕይወትህ ተዓምር ያሰገኝልሃል። ነገር ግን ዝም ብለህ ያገኘሀውን ነገር አታንብብ። ወደ አእምሮ አጸድ የምትለከው ነገር መምረጥ አለብህ። የምታነበው ነገር የመንፈስ ምግብ ሊሆን ይገባል። አንተንም ሕይወትህንም የሚለውጥ ነገር ነው ልታነብ የሚገባህ።

መሳሳት ጥፋት አይደለም። ስህተት የሕይወት አንዱ አካል ከመሆኑ በላይ ለእድገት የግድ አስፈላጊ ነው። ይህን ለማስረዳት አንድ አባባል ልጥቀስልህ። “ደስታ ከመልካም ፍርድ ይገኛል፣ መልካም ፍርድ ደግሞ ከተሞክሮ ይገኛል፣ ተሞክሮ ደግሞ ከመጥፎ ፍርድ ነው የሚገኘው።” ነገር ግን ተመሳሳይ ስህተት በየእለቱ መፈጸም ጥፋት ነው። እንዲህ ያለው ነገር የሚያሳየው ራስን አለማወቅ ነው። ሰው ደግሞ ከእንስሳት የሚለየው ራሱን በማወቁ ነው።

Reviews

There are no reviews yet.

Be the first to review “ራስን ማወቅ”