In Stock

ሕማማት

$15

Categories: ,

Description

ሁሉን የያዘውን ያዙት ፣ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት ፣ የሕያው አምላክን ልጅ አሠሩት ፣ በቁጣ ጎተቱት ፣ በፍቅር ተከተላቸው ፣ በሚሸልተው ፊት እንደማይነገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት።

በሊቃነ መላእክት በመፍራትና በመንቀጥቀጥ በፊት የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት ኃጥአትን ይቅር የሚለውን ኃጥኣተኛ አሉት ፣ በፈራጆች ላይ በሚፈርደው በእርሱ ላይ ፈረዱበት።

ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የእሾክ ዘውድ አቀዳጁት።

ለኪሩቤል ግርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ቀይ ግምጃ አለበሱት።

የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ ለሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊት ተንበረከኩ።

ይህን ያህል ትሕትና እንደምን ያለ ትሕትና ነው?

ይህን ያህል ትዕግስት እንደምን ያለ ትዕግስት ነው?

ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው?

ይህንን ያህል ሰውን ማፍቀር እንደምን ያለ ፍቅር ነው?

ፍቅር የአምላክን ልጅ ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው”

Reviews

There are no reviews yet.

Be the first to review “ሕማማት”